የእድሜዬ በኩሩ ጠሉ ዘሩ ኢየሱስ የሽበቴ ወጉ ሙሉ ክብሩ ኢየሱስ የሞቴ ማረጉ ልኩ ጥጉ ኢየሱስ ያ'ሳቤ መክብቡ መሀሉ እ ስክትሆነኝ አስተምረኝ ስላንተ ማውራት አስተምረኝ ኢየሱስ ማለት ባተሌ ውትርትር ባትሌ ለእንጀራ የምሮጥ 'ንዳይሆን ባዋዋሌ ባተሌ አፈ ባተሌ ኑሬዬ ምግባሬ ጠበኛ ከቃሌ ባተሌ ሆኜ እንዳልሞት የመኖርን ትርጉም እንዳልስት በማለዳ አስተምረኝ ስላንተ ማውራት አስተምረኝ ኢየሱስ ማለት አስተምረኝ ነፍሴን ቀብድ አስይዤ ኢየሱስን መስበክ ስሜን አደብዝዤ የልጅህ ስም ማድመቅ የቃል ሰይፍ መዝዤ መንፈስህ ማላቅ በአፌ ስምህን ይዤ ለአለም ማሳወቅ ባተሌ ሆኜ እንዳልሞት የመኖርን ትርጉም እንዳልስት በማለዳ የእድሜዬ በኩሩ ጠሉ ዘሩ ኢየሱስ የሽበቴ ወጉ ሙሉ ክብሩ ኢየሱስ የሞቴ ማረጉ ልኩ ጥጉ ኢየሱስ ያ'ሳቤ መክብቡ መሀሉ እስክትሆነኝ አስተምረኝ ስላንተ ማውራት አስተምረኝ ኢየሱስ ማለት