Song Lyrics

ጥገኛ ነኝ

Tigegnah negn

ብርኩማዬ የራስ ድጋፍ የሚያስጥል ከሰይጣን አፍ የሚመልስ ነፍስን የሚሳርፍ ክፉውን ከልክሎ የሚሳልፍ ልክ እንዳንተ ሌላ ማውቀው ስሌለኝ እግዚአብሔር እኔ ልጅህ ጥገኛ ነኝ የዘላለም የዘላለም የዘላለም ጥገኛህ የዘላለም የዘላለም የዘላለም ጥገኛህ ሆደ ሰፊ እንደሰማይ እቅዱ ውብ እንደጧት ፃይ ቃሉን ሲክድ የማይታይ ሁሉን ገዢ ያለከልካይ ካንተ ውጪ ሌላ ማውቀው ስለሌለኝ እግዚአብሔርን እኔ ልጅህ ጥገኛህ ነኝ የክፉ ቀን ፈጥኖ ደራሽ የደስታን ቀን ሚሆን ደጋሽ ከሀጥያት መርዝ ፍቱን አርካሽ ከዘላለም ህይወት አድራሽ ካንተ ውጪ ሌላ ማውቀው ስለሌለኝ እግዚአብሔርን እኔ ልጅህ ጥገኛህ ነኝ የዘላለም የዘላለም የዘላለም ጥገኛህ ነኝ የዘላለም የዘላለም የዘላለም ጥገኛህ ነኝ መደሰቻ እንደድል ዋንጫ ሚያዘምረኝ ኢየሱስ ነህ ውስጤን በሀሴት የምትሞላኝ እስቃለሁ በህልውናህ አቅሌን ስቼ በመንፈስህ ከምድር ስበት ተነስቼ ሲከፋኝም አንተው ጋር ነው የማለቅሰው ሳልደባብቅ የጓዳዬን የማወራው አትታዘብ ወይ አትተወኝ ብወድቅብህ ወጌሻህ ነኝ ትለኛለህ በቃልህ ተማሪ ልብ አለኝ ሚጠይቅህ ምንንም ለማድረግ ሚፈልግህ የምክርህ ጥገኛ የትምህርትህ ማያፍር ማይሰለች እርዳኝ ሊልህ ጥገኛህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection