Song Lyrics

አሻግረኸናል

Bezu Mulugeta
Eyesus Liyu New Alin Endegena
አሻግረኸናል ባሕሩን ከፍለህልናል ውሃውን ፈታችን ሆነህ ስትመራን ማንም አልቻለም ሊያቆመን አረ እንዳንተ ያለ በሰማይ ማን ነው ይፈለግ የበላይ ምድርና ሞላው ያንተ ነው ለሕዝብ ሞገስ የሆንከው ችግራችን የአንተ ችግር ሃዘናችን የአንተ ሀዘን ነበር ለካ የኛ ጌታ ምትክ ሆንከን በኛ ፈንታ እስከ መስቀል ወደድከን ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገርን ተሸከምነው የኛን በደል ፡፡ለዘላለም ኢየሱስ ክበር (2x) ስንደክም ስትበረታ ስንወድቅ ሲታገለን ማን ነው እንዳንተ የቻለን አለሁ ያለ ያልታዬን ወረት ከቶ የማያውቅ ኢየሱስ ብቻ ተባረክ (4x) ሆድ ሲብሰን ይገባሃል ብሶታችን ይሰማሃል ከስትንፋስ ይልቅ ቅርብ ነህ ለእኛ አንተ ታስባለህ ከናት በላይ አሳዳጊ ትዕግሥተኛና አሳላፊ የተጐዳን አስታማሚ ሰው አድርጐ ለክብር ሿሚ ባሕሩ ሲቆም ፊታችን ፈርኦን ሲሮጥ ኋላችን አንተ ነህ ለእኛ የደረስክ ውሃውን ለሁለት የከፈልክ ልባችን በአንተ አረፈ አሳዳጃችን አፈረ መርጦናል ባንተ መደገፍ በምንም ነገር ብናልፍ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection