Song Lyrics

አምልኮዬ

Bezu Mulugeta
Eyesus Liyu New Alin Endegena
በወሬ አይደለም እኛ የሰማነው በሕይወታችን እልፍ ጌታ አደረገው ልዩ አፍቃሪ ወዳጅ አባት እግኝተናል ልናመልክ ልንሰግድ በፊቱ ወጥተናል ላምልከው እያልኩኝ እወደዋለሁኝ የመስቀሉን ሚስጥር ፍቅር እያየሁኝ ውለታው ስለእኔ እጅግ በዝቶልናል እኔ አበዛለሁ ለሥሙ ምስጋና እርሱ ብቻ አምላክ አባት ሆኖአልና ይገባል ለስሙ አምልኮ ምሥጋና ስጡት ከልባችሁ አብዙለት ዘምሩ ብቻውን ይመለክ ይወራለት ክብሩ የተነሱበትን ጥሎ አዋረዳቸው ሥልጣኑን ቀምቶ ባዶ አደረጋቸው እነማን በርትተው እግዚአብሔርን ሻሩ እርሱ እኮ ይኖራል በነበረ ክብሩ ሥልጣኑ እጅግ ትልቅ ነው ፈቅጄ እመልከዋለሁ ወድጄ እምበረከካለሁ ልናገር ከምችለው በላይ ትልቅ ነው የክንዱ ሥልጣን ገብቶኛል እዘምራለሁ ሥልጣኑ ከማንም በላይ ነው ስልጣኑ ኃያል ነን ጐበዝ ነን እያሉ በእርሱ ላይ ብዙ ፎረኩ ታገሰ ዘመን ሰጣቸው ታበዩ ክንዱ አጠፋቸው በዘመኑ በታሪክ የለም ስላጣኑ ፍፁም አልተሻረም እንዴት ልናወጥ እንዴትስ ልፍራ እያየሁ የክንዱን ስራ ተደላድዬ ቆሜያለሁ ኃያሉን ክንዱን ይዣለሁ ሊሰራ እርሱ ሲነሳ እያየሁ ሁሉም ይታዘዛል ስልጣኑ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection