Song Lyrics

የተወጋ ጐኑን

Bezu Mulugeta
Eyesus Liyu New Alin Endegena
አዝ፦ የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል መቃብር አትሂዱ የሱስ በዚያ የለም ሕያው ሆኗል እሱ ሕያው ለዘላለም እጆቹን ነክቸ እኔ ፈውስ አገኘሁ ስለዚህ ተነስቷል ተነስቷል እላለሁ አዝ፦ የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል ዐይኖቸ አይተውታል ኢየሱስ ተነስቷል በልብ ጓዳዬ በኑሮዬ ገብቷል አትፍራ ብሎ አለኝ ዳሰኝ ቅረብና አዎ ሕያው ሆኗል ኢየሱስ እንደገና አዝ፦ የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል ዛሬስ አምሮበታል ባባቱ ቀኝ አለ ሁሉን በመታዘዝ ስለተቀበለ ከሥም ሁሉ በላይ ስምም ተሰጥቶታል ፍጥረት ሁሉ የሱስ ጌታ ነህ ይሉታል አዝ፦ የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል ተስፋ እንደሌለው እንበታተንም ሰብሳቢ ቃል አለው እኛ አንወድቅም የሞተ የማይሰማ አምላክ አናመልክም ይሰራል ተነስቷል ሕያው ነው ዘላለም አዝ፦ የተወጋ ጐኑን እጆቼ ሲነካ እይኖቼ በሩልኝ ሕይወት አለው ለካ እንደሞተ አልቀረም ኢየሱስ ተነስቷል ለሞተው ነገሬ ሕያው ነፍስን ዘርቷል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection