Song Lyrics

የመከራው ዘመን

Bezu Mulugeta
Eyesus Liyu New Alin Endegena
የመከራው ዘመን ሁሉ አለፈና ኢየሱስ ልዩ ነው አልን እንደገና ሃሌሉያ እሰይ አሜን አሜን አልን ኢየሱስን ይዘን አሸናፊ ሆንን (2x) ከቁጣው ጢስ ወጣ ፍርድ ከርሱ በራ አሳትም ነደደ ከሰማይ ወጣና በኪሩቤል ሆኖ በፍጥነት በረረ የጠላቴን ሰፈር ገባ እየሰበረ (2x) ፍላጻውን ላከ ሁሉን በተናቸው በመብረቁ እሳት ጌታ አወካቸው ቋጠሮውን ውሉን ጌታዬ ፈታታው የፎከረን ጠላት መደበቂያ አሳጣው (2x) ለወይኔ አጥር ጌታ ክብር ሆኖ ጠላቴን በክንዱ በኃይሉ በትኖ ይኸው ለዚህ እለት ልንበቃ ችለናል መከራችን ሁሉ እንደጉም ተነስቷል/በኢየሱስ ተነስቷል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection