የበግ መንጋ ስጠብቅ ስሙን በዜማ ሳደንቅ ልዑል አየና ከሰማይ ልቡ አረፈ በእኔ ላይ እንዴት ያለ ዓይን አለው (2x) ከሰው ልጆች ልዩ ነው ሃሌሉያ (3x) ደካማነቴንም አውቆ አንበሳውን ለእኔ ለቆ ጠላቴ ብዙ ሲሞክር መጋጋውን ሰባብሮ የረዳኝ እግዚአብሔር ነው (2x) በዝማሬ ላመስግነው ሃሌሉያ (3x) ሀይልንም የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቀና አጽንቶ የሚያቆመኝ ጠላቴንም የሚረታ በአማላክት መካከል እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው ክብሬ ትዘምርለት ማዳኑ ለልጅ ልጅ ነው ሃሌሉያ (3x) በሥጋ ታናሽ ብመስልም ጐልያድ በእኔ ቢስቅም የታመንኩበት ጌታ ነው በጠጠር የሚዘረጋው እኩያ አቻ የሌለው ብርቱ አምላክ እግዚአብሔር ነው (2x) ሃሌሉያ (3x) ተመስገን (3x)