ያለፍነውን ያሳለፈን አረማነው ዮርዳኖስን የከፈለው አረ ማነው ማነው (2x) አረማነው (2x) እግዚአብሔር ነው ብርቱ ሃያል እግዚአብሔር ነው በሰልፍ ኃያል (2x) ኃጢአታችን እጅግ በዝቶ ነፍሳችንን አስጨንቆ መንፈስ ቅዱስ በኛ አዝኖ ሀይወታችን ተበላሽቶ የተቤዥን በምህረቱ ያስታረቀን ከአባቱ የዘላለም ጠባቂያችን ኢየሱስ ነው እረኛችን እንደ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚችለን ማንም የለም በባዕድ ምድር ስንጨቆን ስንገዛ በፈርኦን መከራችን የተሰማው ሃዘናችን ያሳዘነው እስራትን የሰበረ ቀንበሩንም የሰበረ ባለድሎች ያደረገን መልካም ነገር ያጠገበን እንደ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚረዳን ማንም የለም የእኛን መውደቅ የተመኙ ጉድጓዳችንን የቆፈሩ በእጃቸው ተንኮል ይዘው ወጥመዶችን ለእኛ አጥምደው ዛሬ ነገ ጠፋ ያለ የኛን ረዳት ያላወቁ እጃቸውን በአፋቸው አድርገዋል በስራቸው እንደ እግዚአብሔር ለዘላለም የሚያጸናን ማንም የለም