Song Lyrics

ለአንተ ጌታ

Bezu Mulugeta
Eyesus Liyu New Alin Endegena
አዝ፦ ለአንተ ጌታ አያቅትህም ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (2x) ግራ ቀኝ ለሚል ጭንቀት ለያዘው ፈውስን ፈልጐ በለቅሶ ላለው ደርሶ የሚፈውስ የሚታደገው ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ነው አዝ፦ ለአንተ ጌታ አያቅትህም ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (2x) በገዢ ቁጣ ልቡ ለራደ ስፍራውን ሲለቅ ሸርተት ላለ የንጉሥ ልቡ በእጁ ይሆነው አጽንቶ የሚያቆም መድሃኒያለም ነው አዝ፦ ለአንተ ጌታ አያቅትህም ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (2x) በባዕድ ምድር በእስር ላለ ተስፋዬ አሁንስ ማን ነው ለሚለው የእስራአኤል ብርታት ረዳት የሆነው እስረኛን ፈቺ እግዚአብሔር ነው አዝ፦ ለአንተ ጌታ አያቅትህም ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (2x) በሰማይ በምድር የሌለው መሳይ ለተዋረደ ክብርን የሚያሳይ እንደ ኢየሱስ አረ ማን አለ ሁሉንም መስራት ማድረግ የቻለ አዝ፦ ለአንተ ጌታ አያቅትህም ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (2x) እጅህ ስትሰራ ማየት ለጓጓው ተነስ እያለ ፊትህ ላነባው በእሳት መልሰህ ታሳየዋለህ ጠላቱን ጌታ ታሳፍራለህ አዝ፦ ለአንተ ጌታ አያቅትህም ለአንተ ፈውስም አይሳንህም (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection