አዝ፦ ብዙ ትቶልኛል ብዙ ወደዋለሁ ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ ገበናን ሰው መግለጽ ይወዳል ኃጢአትን መቼ ይቅር ይላል የኔ ወድ ከዚህ ሁሉ ልዩ ምሮኛል ሰዎች ይህን ስሙ አዝ፦ ብዙ ትቶልኛል ብዙ ወደዋለሁ ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ ስንቆም ሞገስ የሚያላብሰን ጻድቃኖች አድርጐ የቆጠረን ኢየሱስ ብዙ ትቶልናል ምህረቱ ዛሬም ያኖረናል አዝ፦ ብዙ ትቶልኛል ብዙ ወደዋለሁ ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ ለመውገር ሁሉ ይቸኩላል ድንጋዩን በእጅ ተሸክሟል ኢየሱስ የሰው ድካም ያውቃል ካመድ ላይ ምስኪኑን ያነሳል አዝ፦ ብዙ ትቶልኛል ብዙ ወደዋለሁ ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ ውለታው ለእኔ በዝቶብኛል ነውሬን የሱስ ወስዶልኛል ውበቴ ድምቀቴ ሽታዬ ጠረኔ ሆነልኝ ጌታዬ አዝ፦ ብዙ ትቶልኛል ብዙ ወደዋለሁ ብዙ እኔን ምሮኛል ብዙ አከብረዋለሁ በብዙ ምሥጋና ፊቱ እቀርባለሁ በብዙ ዝማሬ ጌታን አከብራለሁ