አዝ፦ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (2x) እግዚአብሔር ድንቅ ነው ፈርኦን ሊገዛ እስራኤልን ልቡን አደንድኖ ከፍ ቢልም ሕዝቡን ለመታደግ የቆረጠው የሰራዊት ጌታ አሸነፈው አዝ፦ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (2x) እግዚአብሔር ድንቅ ነው ዳንኤል ቢጣልም በጉድጓዱ አንበሳ እንዲበላው ቢታዘዝ የኃያላን ሀያል ኢየሱስ አዳነ ካንበሳው ባሪያውን አዝ፦ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (2x) እግዚአብሔር ድንቅ ነው መከራ ቢከበን ዙሪያችን ተቆረጠ ስንል ተስፋችን በከፍታዎች ላይ ከፍ የሚል ልዑል አምላካችን ባለድል አዝ፦ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (2x) እግዚአብሔር ድንቅ ነው አይሆንም ተብሎ ተቆርጦ ተስፋዬ በሙሉ ተሟጦ እግዚአብሔር ቃሉን አሰበ ነገር በጊዜው ጨኮለ አዝ፦ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (2x) እግዚአብሔር ድንቅ ነው አፍ ባለው ነገር ላይ ከፍ ብሎ በከፍታዎች ላይ ድንቅ ሆኖ የኖረ ሳይረታ ዘላለም እግዚአብሔርን የሚመስል የለም አዝ፦ እግዚአብሔር በከፍታው ድንቅ ነው (2x) እግዚአብሔር ድንቅ ነው