በሌሊትም ከልቤ ጋር ተጫወትኩኝ ነፍሴንም አነቃቃኋት ጌታን አሰብኩኝ እርሱን ሳስብ ልቤ በደስታ ሁሌ ይሞላል ያስጨነቀኝንም ሁሉ ጌታ ይጥላል እግዚአብሔርን ሳየው ደስ አለኝ እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስ አለኝ እርሱን ተመልከቱ ያበራላችኋል (2x) የጨለመውንም ጌታ ይገፈዋል (2x) ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችኋል የጨለመውን ጌታ ይገፈዋል (2x) ለተጨነቀ ሰው ጨለማ አይሆንም ብሏል በእውነት ለሚታመኑት ልቡ ይራራል አሁንም ተስፋዬም ትዕግሥቴም በእርሱ ነው በዘመኔ እያሰብኩት እደሰታለሁ እግዚአብሔርን ሳየው ደስ አለኝ እግዚአብሔርን አሰብኩት ደስ አለኝ እርሱን ተመልከቱ ያበራላችኋል (2x) የጨለመውንም ጌታ ይገፈዋል (2x) ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችኋል የጨለመውን ጌታ ይገፈዋል (2x) ስትፈለግ የምትገኝ አንተ ነህ ምታጽናና ምትደግፍ ወዳጅ ነህ በብርሃንህ ብርሃን እንዳይ አደረከኝ በቀረብኩህ ቁጥር ጌታ አበራህልኝ አንተ ሙሉ ነህ እታመንሃለሁ ዓይኔን ከሰው ላይ ይኸው አንስቻለሁ አንተ ብቻህን በቂ ነህ አንተ ብቻህን (2x) አንተ ብቻህን ሙሉ ነህ አንተ ብቻህን (2x) አንተ ሙሉ ነህ እታመንሃለሁ ዓይኔን ከሰው ላይ ይኸው አንስቻለሁ አንተ ብቻህን በቂ ነህ አንተ ብቻህን (2x) አንተ ብቻህን ሙሉ ነህ አንተ ብቻህን (2x)