አዝ፦ ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው በቃልህም ልቤን ደስ አለው የደስታዬ/የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ መተኪያና እኩያ የለህ (2x) ቃልህን እወደዋለሁ (2x) ድምጽህን እወደዋለሁ (2x) የእግዚአብሔር ቃሉ የነጠረ ነው ለሚታመኑበት እርሱ ጋሻ ነው ለቃልህ ጌታዬ እኔም እገዛለሁ ሁኚ ያለኝን ሁሉ ዛሬም እሆናለሁ ያፅናናኝን የደረሰልኝን በመንገዴ ሁሌ የሚመራኝን ሕይወቴንም ለቀየረልኝ ቃልህ ብቻ ሁሌ አስተማማኝ አዝ፦ ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው በቃልህም ልቤን ደስ አለው የደስታዬ/የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ መተኪያና እኩያ የለህ (2x) ቃልህን እወደዋለሁ (2x) ድምጽህን እወደዋለሁ (2x) ከአፍህ የሚወጣው ሕያው የአንተ ቃል መሻት ግን ወደ እኛ ስቦ ያመጣል ያድናል ይገላል ይተክላል ይነቅላል እርሱ ያለው ብቻ በእርግጥም ይሆናል ሳር ይደርቃል አበባው ይረግፋል በምድር ያለው ሁሉ ይለዋወጣል ዘመን ጊዜ የማይለዋውጠው የአምላኬ ቃል ፀንቶ የሚኖር ነው አዝ፦ ብዙ ምርኮ እንዳገኘ ሰው በቃልህም ልቤን ደስ አለው የደስታዬ/የሰላሜ ምንጭ አንተ ነህ መተኪያና እኩያ የለህ (2x) ቃልህን እወደዋለሁ (2x) ድምጽህን እወደዋለሁ (2x)