ከሆነልኝ ነገር ሁሉ ይልቅ ያረከው አንተ ሆንክልኝ ድንቅ (2x) ስለዚህ ትበቃኛለህ ሁልጊዜ ታስመካኛለህ (2x) የከበደኝን ሁሉ አንተ አቀለልከው ፀሎቴንም እየሰማህ ጥያቄዬን መለስከው ለሰው ልጆች መልካምን በማድረግ ደስ ይልሃል ልዩ ነህ የእኔ ጌታ ማንስ ይመስልሃል ስለዚህ ትበቃኛለህ ሁልጊዜ ታስመካኛለህ (2x) በዕድሌ እኮ አይደለም በደረሰኝ እጣ ምታኖረኝ እግዚአብሔር ነህ ሁሌ ባለጠጋ በክንዶችህ ተማምኜ በጥላህ አድራለሁ ጥጋቤ ነህ እርካታዬ አርፌብሃለሁ አዝ፦ ስለዚህ ትበቃኛለህ ሁልጊዜ ታስመካኛለህ (2x) በልቤ ውስጥ ያለው ሞልቶ የፈሰሰው (2x) በውስጤ ያረከው የፍቅር እሳት ነው (2x) ይህንን አይቼ እንዴት ዝም እላለሁ (2x) በአዲስ በአዲስ ዜማ አመሰግናለሁ (2x) የእኔ ጌታ ተባረክልኝ (3x) ሌላማ ምን እልሃለሁ ተባረክልኝ (2x) ሰልፉን ለአንተ ሰጠሁ እኔ እቆማለሁ (2x) ቸርነት ምህረትህን ሁሌ እናገራለሁ (2x) ድብቅ ጦር አንስተህ ጠላቴን መተሃል (2x) ድል አድራጊው ኢየሱስ ክብር ይገባሃል (2x) የእኔ ጌታ ተባረክልኝ (3x) ሌላማ ምን እልሃለሁ ተባረክልኝ (2x) ታማኝነትህን ሁሌ አወራለሁ ቸርነትህ ዘለዓለም ዘምራለሁ (2x) ሌላማ ምን እልሃለሁ ጌታዬ ሳከብርህ ያኔ ረካለሁ አምላኬ (2x) ታማኝነትህን ሁሌ አወራለሁ ቸርነትህ ዘለዓለም ዘምራለሁ (2x) ሌላማ ምን እልሃለሁ ጌታዬ ሳከብርህ ያኔ ረካለሁ አምላኬ (2x)