Song Lyrics

ወጀቡ

Bethlehem Wolde
Kalihin Wededkut
አንተን የታመነ መች አፈረ አንተን የታመነ መች ከሰረ አምላኬ ሆይ ብርቱ መታመኛዬ ነህ ኢየሱሴ ብርቱ መታመኛዬ ነህ አምላኬ ሆይ ብርቱ መታመኛዬ ነህ ኢየሱሴ ብርቱ መታመኛዬ ነህ (2x) ትላንትን አልፌ ዛሬ ደርሻለሁ ደርሻለሁ ዛሬ ደርሻለሁ (2x) ቅኝህ ደግሞኛል ለነገ አምንሃለሁ አምንሃለሁ ለነገ አምንሃለሁ (2x) ምን ያስደነግጣል ለምን እሰጋለሁ እሰጋለሁ ለምን እሰጋለሁ (2x) ተሻገሪ ያለኝ ጌታ ከእኔ ጋር ነው ከእኔ ጋር ነው ጌታ ከእኔ ጋር ነው (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር አለ አለ አለ አምላኬ አለ አለ አለ በኃይሉ አለ አለ አለ በሥራው አለ አለ አለ እኔም አየሁት አለ አለ ሲደርስልኝ አለ አለ ጠላቴን ረግጦ አለ አለ ሲወጋልኝ አለ አለ ወጀቡ ቢበዛ ነፋሱም ቢያይልም ቢያይልም ነፋሱም ቢያይልም (2x) ቃሉን እይዛለሁ አልነቃነቅም አሃ አልነቃነቅም (2x) ቃል ይናገር እንጂ ቃሉን የሚጠብቅ አሃ ቃሉን የሚጠብቅ (2x) ከሁኔታ በላይ አምላኬ ነው ትልቅ አሃ አምላኬ ነው ትልቅ (2x) ክበር ዛሬ እንደገና (3x) ልርካ ክብርህን ልይና ልጥገብ ክብርህን ልይና ልጥገብ ክብርህን ልይና (2x) ለፈተና መውጫ አዘጋጀልኝ አሃ አዘጋጀልኝ (2x) ለማዕበሉ ደግሞ ገደብ ሰራልኝ አሃ ገደብ ሰራልኝ (2x) የእኔ ነገር እርሱን ይመለከተዋል አሃ ይመለከተዋል (2x) ስለ እኔ ተዋግቶ አሸንፎልኛል አሃ አሸንፎልኛል (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር አለ አለ አለ አምላኬ አለ አለ አለ በኃይሉ አለ አለ አለ በሥራው አለ አለ አለ እኔም አየሁት አለ አለ ሲደርስልኝ አለ አለ ጠላቴን ረግጦ አለ አለ ሲወጋልኝ አለ አለ የዮርዳኖስ ጩኸት ዝም ብሎ እያጓራ (3x) አምላክን ጥራ እንጂ አትደንግጥ አትፍራ (3x) ዮርዳኖስ ፉከራው እስክትረግጠው ነው (3x) አይዞህ በእምነት ግባ ያዘዘህ ጌታ ነው (3x) ክበር ዛሬ እንደገና (3x) ልርካ ክብርህን ልይና ልጥገብ ክብርህን ልይና ልጥገብ ክብርህን ልይና (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection