Song Lyrics

እረኛዬ

እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ የነፍሴ ጠባቂ አንተ የማትተኛ እኮራለሁ ባንተ እመካለሁ በምንም አልፈራም በምንም አልሰጋም የነፍሴ ንጉስ ኢየሱስ አንተ ለኔ እረኛዬ ነህ ነፍሴን ከአዳኝ ወጥመድ ዘወትር ትጠብቀኛለህ አንተ የኔ እረኛ አትተኛም አታንቀላፍም በሰላም ውዬ አድራለሁ እኔ በምንም አልሰጋም እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ……… ካንተ ሌላ ወዳጅ ካንተ ሌላ እረኛ ለኔስ ምንም የለኝ አንተ የማትተኛ መልካም እረኛ ኢየሱስ ስለኔ ነፍሱን ሰጥቶኛል ሰላሙ ልቤን ሞልቶ በድል ያራምደኛል እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ……… በለመለመ መስክ ዘወትር ያሳድረኛል በእረፍት ውሀ ዘንድ ጌታ እኔን ይመራኛል ቸርነት ምህረቱ እየተከተሉኝ ከክፉ ይጠብቁኛል በድል ያራምዱኛል እረኛዬ አንተ የኔ እረኛ……… ምድር ብትነዋወጥ ብትነዋወጥ ሁሉም ነገር ስፍራውን ቢለቅ ከቶ እንዳልፈራ ከቶ እንዳልናወጥ ልቤን ሞላኸው በሰላም በእረፍት ያረጋጋኸኝ በነውጡ አለም ጋሻዬ ነህና ለዘለአለም እኔ ልበልህ እረድኤቴ ስለሆንክልኝ አቅም ጉልበቴ እልሀለሁ እረድኤቴ(6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection