Song Lyrics

ራርቶልናል

Bethlehem Wolde
Kalihin Wededkut
አዝ፦ እራርቶልናል (4x) ቸር ነውና መቼ ይተውናል ቸር ነውና መቼ ይረሳናል (2x) ለረዳን እንዲህ ላቆመን (2x) በየዕለቱ ለሚመራን (2x) ነፍሳችንን እያፈሰስን (2x) ከእግሮቹ ሥር እንሰግዳለን (2x) አዝ፦ እራርቶልናል (4x) ቸር ነውና መቼ ይተውናል ቸር ነውና መቼ ይረሳናል (2x) ባሕሩንም በሥልጣን አዞ (2x) ፀጥ አረገው በመሃል ገብቶ (2x) ስንጨነቅ የሚራራልን (2x) አባት አለን የሚያስብልን (2x) እርሱ ስለ እኛ/እኔ ያስባልና ያስባልና ተራራውንም ሜዳ አድርጓልና አድርጓልና (2x) ዛሬም አምነዋለሁ ነገም አምነዋለሁ ዘለዓለም አምነዋለሁ (2x) ያስጨነቀኝ ጠላቴ አላነቃንቅ ያለኝ እየተከታተለ እረፍትን የሚነሳኝ የአምላኬ ቃል ሲመጣ ራርቶ ዘንበል ሲልልኝ ፊቴ የቆሞው ተራራ ደልዳላ ሜዳ ሆነልኝ (2x) እርሱ ስለ እኛ/እኔ ያስባልና ያስባልና ተራራውንም ሜዳ አድርጓልና አድርጓልና (2x) ዛሬም አምነዋለሁ ነገም አምነዋለሁ ዘለዓለም አምነዋለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection