ምሥጋናን የሚሰዋ ያከብረኛል ያከብረኛል ብለሃል እሰዋለሁ ምሥጋናዬ ይኸው እሰዋለሁ አምልኮዬ ይኸው (2x) ምሥጋናን በአፌ የጨመርክ ምሬትን ከእኔ ያስወገድክ አምላኬ አንተ ነህና ይብዛልህ ዛሬም ምሥጋና ይገባሃልና አሜን ይገባሃልና እናመልክሃለን እናመልክሃለን ከዙፋንህ ስርም እንሰግድልሃለን እናመልክሃለን እናመልክሃለን በእውነት በመንፈስ እንሰግድልሃለን ክብርህን ላውራ ጌታዬ ሞገስ ያግኝ ምሥጋናዬ ሳከብርህ ሁሌ ደስ ይለኛል እረካለሁ ክብርህ ያጠግበኛል ክብርህ ያጠግበኛል አሜን ክብርህ ያጠግበኛል እናመልክሃለን እናመልክሃለን ከዙፋንህ ስርም እንሰግድልሃለን እናመልክሃለን እናመልክሃለን በእውነት በመንፈስ እንሰግድልሃለን ድል በመንሳቱ ለሚያዞረኝ በጠላቶቼ ዕራስ ላይ ላቆመኝ እዘምራለሁ ለጌታ እዘምራለሁ አሃ እዘምራለሁ ለአምላኬ እዘምራለሁ ኦሆ ያስጨናቂውን ዘንድ ጌታዬ ሰባበርከው ግዙፉን ቀንበሬን ከላዬ አስወገድከው ሁሌ እደነቃለሁ ጌታዬ በማዳንህ ባለህ ምሥጋና ላይ ሌላም ልጨምርልህ (2x) ዝናህን አወራለሁ (3x) ማዳንህን እናገራለሁ ዝናህን አወራለሁ (3x) ማዳንህን እናገራለሁ ጣላቴ ይዞራል የሚውጠው ፈልጐ ምንም ላይሞላለት ሁሌ መናውን ቀርቶ እኔን ግን ጌታዬ ከድል ድል ያዞረኛል ጠላቴን ከእግሬ ስር ጌታዬ አስረግጦኛል (2x) ጠላቴ ዕልል አይልብኝምና እንደወደድከኝ አወቅሁ እንደመረጥከኝ አወቅሁ (2x) በእኔ ድንኳን ዕልልታ ይሰማዋል ዝማሬ ይሰማዋል የወደደኝ ጌታ ይህንን አድርጓል የመረጠኝ እርሱ ይህንን አድርጓል የማንም ባለዕዳ ያልሆነው እግዚአብሔር አፈራረሰና የጠላቶቼን ምክር አዳዲስ ዝማሬ በአፌ ውስጥ ሲጨምር የነፍሴ ቅኝቷ ሁሌ ክብር ክብር (2x) ዝናህን አወራለሁ (3x) ማዳንህን እናገራለሁ ዝናህን አወራለሁ (3x) ማዳንህን እናገራለሁ ክበር ከሚሉህ ጋር ንገሥ ከሚሉህ ጋር (2x) እስማማለሁ እኔም እጨምራለሁ (4x) ክበር ከሚሉህ ጋር ንገሥ ከሚሉህ ጋር (2x) እስማማለሁ እኔም እጨምራለሁ (4x)