Song Lyrics

ታምራትን

ብቻህን ታምራትን አንተ ትሰራለህ የማመልክህ እግዚአብሔር አንተ ሁሉንም ቻይ ነህ (2x) ደመና ሳታሳይ ዝናብ ታዘንባለህ ከደረቀው አለት ውሃ ታፈልቃለህ በቃልህ ስታዝዘው ሁሉ ይታዘዝሃል የፍጥረት ገዢ ነህ ማንስ ይመስልሃል ብቻህን ታምራትን አንተ ትሰራለህ የማመልክህ እግዚአብሔር አንተ ሁሉንም ቻይ ነህ (2x) ጌታ ኢየሱስ ለኔ እጅግ ልዩ ነህ ለሰው ሁሉ ወዳጅ ሁሉ የተቻለህ እኔም ባንተ ጌታ እተማመናለሁ ሞትንም ወስደሃል እኮራብሃለሁ ብቻህን ታምራትን አንተ ትሰራለህ የማመልክህ እግዚአብሔር አንተ ሁሉንም ቻይ ነህ (2x) ማንም ሳያቅትህ ማንም ሳይመክርህ ዓለምን ሞላዋን አንተ መሠረት ወብና ድንቅ አርገህ እኛን ፈጥረኸናል የእጆችህ ስራዎች አመስግነንሃል በተስፋ ለሚጠብቁት ለምትሻውም ነፍስ ጌታ መልካም ነው ይሰጣል እረፍት እርሱን ታምኖ ጠብቆ ያፈረ ማነው ጸሎቴን ሰምቷል ጌታን ላክብረው ዛሬም ላሞጋግስህ ክበርልኝ ክበርልኝ ውለታህን ልቁጠረው ንገሥልኝ ንገሥልኝ ጸሎቴን ሰምተሃል ክበርልኝ ክበርልኝ ጠላቴን ረግጠሃል ንገሥልኝ ንገሥልኝ ከፍ በል ዝማሬ ይድረስህ ሌላማ የለኝም የምሰጥህ (2x) ጌታን የሚጠብቁ ቅዱሳን ሁሉ ከመልካም ነገር አንዳች አይጐድሉ እኔም በዘመኔ ተጠግቼዋለሁ ከመልካም ነገር ሁሌ እጠግባለሁ ዛሬም ላሞጋግስህ ክበርልኝ ክበርልኝ ውለታህን ልቁጠረው ንገሥልኝ ንገሥልኝ ጸሎቴን ሰምተሃል ክበርልኝ ክበርልኝ ጠላቴን ረግጠሃል ንገሥልኝ ንገሥልኝ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection