Song Lyrics

በከፍታ

የምትሰራውን ስለምትመዝን በሚሆነው ነገር እኔ አላዝን የማመልክህ አምላክ ለኔ ልዩ ነህ ለተገፉት ደራሽ በጸድቅ ትፈርዳለህ አዝ:- በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ ለኔም ምታስበው በጐና መልካም ነው ክፉ ሃሳብ አይደል የሰላም ሃሳብ ነው ከኔ የበለጠ ለኔ ታስባለህ ከእናት ከአባት ይልቅ ትጠነቀቃለህ አዝ:- በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ በወይንም ሐረግ ውስጥ ፍሬ ባይገኝ ትናንት የነበረኝ ዛሬ ባይኖረኝ ማታ ባለቅስ እንኳን ጠዋት እስቃለህ ስለዚህ ሁልጊዜ አንተን አከብራለሁ አዝ:- በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ ሰማዩ ቢጠራ ደመናም ባይኖርም ምልክት ባይታይ ነፋስም ባይነፍስም በገናዬን ይዤ እደረድራለሁ ሸለቆ ሲሞላ በዓይኔ አየዋለሁ አዝ:- በከፍታ በዝቅታ በሃዘንም በደስታ አንተን አከብራለሁ ጌታን አንተን አከብራለሁ አንተን አከብራለሁ ኢየሱስ አንተን አከብራለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection