አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (2x) ለኔ ነው መንከራተትህ መስቀል ተሸክመህ መውረድህ ለኔ የደም ላብ ያላበህ ፍቅር ነው እንዲህ ያስጨነቀህ ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ ከአብ ዘንድ ለኔ የተሰጠ ትልቁ ስጦታዬ አንተ ነህ ይህ ሚስጥር ለኔ ተገልጾ መዳን ከአንተ ዘንድ ሆኖልኛል ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (2x) ልከፍለው አልችልም ውለታህን ያኔ ያረከውን በጐልጐታ ምስጋናን ሙገሳን ይዤ ላክብርህ ኢየሱስ ወዳጄ ውለታህን አስታውሳለሁ ፈቅጄም አመልክሃለሁ ውለታህን አስታውሳለሁ ወድጄም አመልክሃለሁ አዝ:- ባለውለታዬ ጌታዬ የእግዚአብ ሔር ልጅ ኢየሱስ መድህኔ ቅዱስ ስምህን እባርካለሁ ውለታህን አስታውሰዋለሁ (2x)