አምላኬ ሆይ ለስምህ ዘምራለሁ ምሥጋናህ በአፌ ነው በማለዳ ምህረትህን በሌሊትም እውነትህን አወራለሁ . (1) . ስለቆምኩ በፊትህ ክብርህን እንዳወራ አንተን እላለሁ ሁልጊዜ የመረጥከኝም አንተው ነህ ለዚህ ስራ (2x) እስካልወሰድክብኝ እስካለ እስትንፋሴ እስካለ እስትንፋሴ አቀርብልሃለሁ የነፍሴን ውዳሴ የነፍሴን ውዳሴ (2x) ክበርብኝ ክበርብኝ ንገሥብኝ ንገሥብኝ (2x) ዓመታቶችህ አያልቁምና (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ) የዕድሜ መነሻ መጨረሻ (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ) የፍጥረት ንጉሥ የፍጥረት ጌታ (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ) ይሰማ ለአንተ በኩር ምሥጋና (ዘለዓለማዊ ዘለዓለማዊ) (2x) አንተ ጥንትም ነበርክ ዛሬም አለህ ለዘለዓለም ትኖራለህ ተከብረህ/ነግሰህ (4x)