Song Lyrics

ረድኤቴ

Bethlehem Tezera
Yehiwote Balebet
ዓይኖቼን አነሳሁ ወደ ተራሮቹ ይረዱኝ እንደሆን ብዬ ትልቆቹ ታግሼ ጠበኩኝ የቃል ተስፋቸውን ዛሬ ነገ እያልኩኝ ሳይ እጅ እጃቸውን ክረምት አልፎ በጋ ይኸው መጣ ረዳቴ ግን ከየት ከየት ይምጣ አቤቱ ጌታዬ አድነኝ በደጅህ መጣሁኝ መረጥኩኝ (2x) ረድኤቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው ሰማይን ምድርን ከሰራው (2x) እግዚአብሔር ደግ ነው አያሳፍርም ይረዳኛል አምናለሁ አያሳፍርም የጨለመ ቢመስልም አያሳፍርም ጌታ ይመጣል አይቀርም አያሳፍርም (2x) ዓይኖቼን ቀና አድርጌ ያልከኝን አስታውሳለሁ መከራዬን ሀዘኔን ያን ጊዜ እረሳዋለሁ (2x) እዛ ጋር አለው ዋጋ (2x) አንተ ጋር አለው ዋጋ እዛ ጋር አለው ዋጋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection