ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ እንዲሆን የሞገስ ዘውዴ የአንገት ድርዬ ሁሌ ቃልህ ነውና የእግሬ መብራት መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (፪x) አቤቱ እንዳልበድልህ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን መንገድም እንዲነጻልኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን በትዕዛዝህ መንገድ እንድሮጥ ተንሸራትቼም እንዳልገባ ማጥ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ስንፍናን ተግቼ ኃጢአትን ሳላምጥ ሕይወቴ በድንገት እንዳያመልጥ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ስህተትን እንዳስተውላት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን እንድሰወር ከስውር ኃጢአት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ከጓደኞቼ ጋር በሳቅ ጨዋታ መስመር እንዳላልፍ እንዳልረሳ ጌታ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የድፍረት ኃጢአት ጠፍሮ እንዳይዘኝ የቃልህ ፍርሃት ሁልጊዜ እንዲያዘኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (፪x) መፅናናት ሲያስፈልገኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን መከራው ሲያሳድደኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ከጠላቴ ዛቻ ከምክሩ እንዳልፈራ ልቤ እንዲጠበቅ በምክርህ እንድመራ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የኃጥአን ገመዶች ሲተበተቡብኝ አለቆች ተቀምጠው ሲያሙኝ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን በአመፀኞች እንዳልቀና ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የግፍ እንጀራ እንዳልበላ ትዝታዬ ቃልህ ይሁን የጓዳዬን ኑሮዬን ቤቴን ለመሙላት በከንፈሬ እንዳልወሰልት ትዝታዬ ቃልህ ይሁን እግሬ እንዲከለከል ከክፋት ጐዳና በፈተና ሁሉ እምነቴ እንዲፀና ትዝታዬ ቃልህ ይሁን ቃልህ ይሁን ትዝታዬ ቃልህ ይሁን (፪x) ሕግህን እጽፈዋለሁ በልቦናዬ እንዲሆን የሞገስ ዘውዴ የአንገት ድርዬ ሁሌ ቃልህ ነውና የእግሬ መብራት መንገዴን የሚያቀናልኝ በአንተው ስርዓት (፪x)