ይሁን በሚል ቃልህ ብቻ ሰማያት ፀኑ ይሁን በሚል ቃልህ ብቻ ይኸው ዓለሙ አይተን የማንጨርሰውን በእድሜ ልካችን ይሁን ይሁን ብለህ ብቻ አበጀኸልን (2x) የስልጣንህ ቃል ካፍህ ሲወጣ ያልነበረው ወደ መኖር መጣ ታዘዘ ሁሉም ብብልሃትህ አንተ እንዳሰብከው እንዳየህለት (2x) ምንጩ አንተ ነህ የእኔ መገኛ ስኖርም በአንተ የአንተ ጥገኛ ትንፋሼን እንኳን ከአንተ ተውሼ እንዳከብርበት አንተን መልሼ እኔ አላውቀውም የፀጉሬን ቁጥር አንተ ግን ቆጥረዋለህ እኔ አላውቀውም የዘመኔን ልክ አንተ ለክተኸዋል እኔማ በእኔ አልመጣሁም እኔን እኔ አልመራውም እኔነቴን እኔ አልወሰንኩም እኔ የእኔ አይደለሁም (2x) መረጥክለኝ ትውልድ ሀገሬን መረጥክለኝ ዘሬን ጐሳዬን መረጥክልኝ እናት አባቴን መረጥክልኝ መልኬን ፆታዬን ይሁና አንተ ያሰብክልኝ ይሁና የወደደክልኝ ይሁና የመረጥክልኝ ይሁን አሜን ይሁንልኝ (2x) አዝ፦ የህይወቴ ጌታዋ የህይወቴ ተጠሪዋ የህይወቴ ባለቤት እግዚአብሔር ነው በእውነት (2x) ስራ ሰሪውን ለምን እንደዚህ አረከኝ እንደማይለው እኔም ፍጡር ነኝ ጌታ ነው በእኔ የወደደውን ሚያደርገው ሸክላ ሰሪውን ለምን እንደዚህ አረከኝ እንደማይለው እኔም ፍጡር ነኝ ጌታ ነው በእኔ የወደደውን ሚያደርገው ስራ ሰሪውን ለምን እንደዚህ አረከኝ እንደማይለው እኔም ፍጡር ነኝ ጌታ ነው በእኔ የወደደውን የሚያደርገው ሸክላ ሰሪውን ለምን እንደዚህ መልሰኝ ቀልሰኝ አይለውም ስልጣን በእጁ ነው እንደወደደ እንደፈቃዱ ሊያደርገው ቢበላሽም አፍርሶ እንደገና ይሰራዋል ባለቤት ነዋ ሸክላ ሰሪው ሸክላው በእጁ እንዳለ የእኔም ህይወት በእግዚአብሔር እጅ ዋለ (2x) አዝ፦ የህይወቴ ጌታዋ የህይወቴ ተጠሪዋ የህይወቴ ባለቤት እግዚሀብሄር ነው በእውነት (2x) እኔማ በእኔ አልመጣሁም እኔን እኔ አልመራውም እኔነቴን እኔ አልወሰንኩም እኔ የእኔ አይደለሁም (2x) ይሁና አንተ ያሰብክልኝ ይሁና የወደደክልኝ ይሁና የመረጥክልኝ ይሁን አሜን ይሁንልኝ (2x)