መልካም ነህ አንተ የእኔ ጌታ ለሚታመኑህ ጋሻ መከታ አያልቅም ርህራሄህ አልጠፋንም አለንበት (2x) በሕይወት ጐዳና ላይ ደክሞ ለወደቀው ተስፋን ቆርጦ ታነሳዋለህ እንደገና እንዳይጠፋ ወደሃልና አንዳያስብ ዳግም ክፋቱን ታወጣለህ ሃዘን ከልቡ ትረዳዋለህ እስኪፈወስ በጠላቱ አንዳይከሰስ ታነሳለህ ሰው ከወደቀበት ታነሳለህ አለህ ምህረት ታነሳለህ አትጥልም አትተውም ታነሳለህ ቸር ዘለዓለም (2x) የታመነ ደም ነው የኢየሱስ የረከሰን ሁሉ ሚቀድስ ኃጢአት ቢሸት አንደ ደም ቀልቶ ያጠራዋል እንደ ባዘቶ የተጨነቀች ነፍስ መሸሻ ምህረት አለው ፊቱን ለሚሻ ይሞላል አፍን በዝማሬ አስጥሎ ከጨካኙ አውሬ ያነሳል ሰው ከወደቀበት ያነሳል አለህ ምህረት ያነሳል አትጥልም አትተውም ያነሳል ቸር ዘለዓለም ታነሳለህ ሰው ከወደቀበት ታነሳለህ አለህ ምህረት ታነሳለህ አትጥልም አትተውም ታነሳለህ ቸር ዘለዓለም