አዝ፦ ለምን እሩቅ ልሂድ ለምን ጐረቤቴ ፍቅርህን ካየሁት አለሁበት እኔ የፍቅርህ ምሳሌ የመውደድህ ምሳሌ አለሁኝ እኔ የማክበርህ ምሳሌ የማንሳትህ ምሳሌ አለሁኝ እኔ (2x) ምህረትህን አልከለከልከኝም በጠላት እጅ አልዘጋህብኝም ሆነህልኝ የመጠጊያ ቤቴ እረሳሁት ሃዘኔን ምሬቴን ተከተለኝ ቸርነት ምህረትህ ጨመረልኝ የሕይወት ውበት በፍቅርህ ከማደር በቀር ምን ልበል ምን አለ ሌላ ነገር አዝ፦ ለምን እሩቅ ልሂድ ለምን ጐረቤቴ ፍቅርህን ካየሁት አለሁበት እኔ የፍቅርህ ምሳሌ የመውደድህ ምሳሌ አለሁኝ እኔ የማክበርህ ምሳሌ የማንሳትህ ምሳሌ አለሁኝ እኔ ባትመግበኝ እጅህ ምህረትህ እጠፋለሁ ከዓይንህ በቅፅበት የምህረትህ ጥገኛ ናት ነፍሴ ታስፈልገኛለህ እንደ እስትንፋሴ አዘነብከው ፍቅርህን በላዬ አረሰረሰኝ ዘልቆ በጓዳዬ አያልቅብህ አንተስ ደግነት የትልቅ የትንሹ አባት ይነበብ ይነበብ ታሪኬ ይነገር በእኔው አፍ (2x) በእግዚአብሔር ምህረት ተወልጄ በእግዚአብሔር ምህረት ታድጌያለሁ በእግዚአብሔር ምህረት ሮጬ ሮጬ በእግዚአብሔር ምህረት እሄዳለሁ (3x) በእግዚአብሔር ምህረት ተወልጄ በእግዚአብሔር ምህረት ታድጌያለሁ በእግዚአብሔር ምህረት ሮጬ ሮጬ በእግዚአብሔር ምህረት እሄዳለሁ