እረፈደ እረፈደ ጊዜውም ነጎደ እየነደደ እመጣለሁ ስትል ተደስቼ እንደምን ዘገየ የምስራቼ እፈልጋለሁ ቅን ምላሽ ቆይ ካልክ አሁንም ግን ይሁን እሺ እፈልጋለሁ ውብ ምላሽ ቆይ ካልክ አሁንም ግን ዛሬም እሺ (×2) የእግዚአብሔር ጊዜ ከእኔ ጊዜ ይለያል ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር ጊዜ ከሰው ጊዜ አይገጥምም ሁል ጊዜ አ-ሃ ማለዳ ተነስቶ አ-ሃ ህልሙን የተረከ አ-ሃ በወንድሞች ሊጣል አ-ሃ ሊሸጥ መች መሰለው ደሞ ክፉ ዘመን አልፎ እፎይ አረፍኩ ባለበት እንዴት ለእግዚአብሔር ባደረ ምነው የግዞት ቤት ብረት እኔ ምፈልገው ጉዳዬ እንዲሰራ እርሱ ሚፈልገው እኔኑ ሊሠራ እኔ የሚታየኝ የቅርብ የቅርቡ ነዉ እርሱ የሚያይልኝ የዘላለሜን ነዉ እኔ ምፈልገው ቢሆን ዛሬዉኑ እርሱ ሚያስተምረኝ መሆን በእምነት ፅኑ እኔ ምጠይቀው ስለዚች ምድር እርሱ ሚያዘጋጀኝ ለሰማይ ቁምነገር ቢያመኝም እጠብቃለሁ ስጋዬን በጥርሴ ይዤ አንተኑ እታገሳለሁ ለሀሳብህ እጅ ሰጥቼ (×2) አ-ሃ ከበግ እረኝነት አ-ሃ ተጠርቶ ሊቀባ አ-ሃ ይመስል ነበረ አ-ሃ ማለዳው የካባ ደርሶ ሀገር አሳርፎ እልፍ ገዳይ ሲባልለት ምነው በከበሮ ማግስት ህይወት ሰልፍ ሆነበት እኔ ምፈልገው ጉዳዬ እንዲሰራ እርሱ ሚፈልገው እኔኑ ሊሠራ እኔ የሚታየኝ የቅርብ የቅርቡ ነዉ እርሱ የሚያይልኝ የዘላለሜን ነዉ እኔ ምፈልገው ቢሆን ዛሬዉኑ እርሱ ሚያስተምረኝ መሆን በእምነት ፅኑ እኔ ምጠይቀው ስለዚች ምድር እርሱ ሚያዘጋጀኝ ለሰማይ ቁምነገር ቢያመኝም እጠብቃለሁ ስጋዬን በጥርሴ ይዤ አንተኑ እታገሳለሁ ለሀሳብህ እጅ ሰጥቼ (×2)