ሰው ሰውን ይወዳል ይቀርባል ለጥቅሙ ቢጤውን ፈልጐ እንዳሳቡ እኔን ግን የገረመኝ የደነቀኝ እ/ር ወዶኛል እንዲሁ እንዲሁ ( 2x) ተሰማ ምስራቹ ሜዳ ባደሩ በእረኞቹ ወንጌሉ ተሰበከ ባልተማሩ ዓሣ አጥማጆች ቢሉትም ግብዞቹ ያሃጢያተኞች ዋና ወዳጅ እልቀረም ሳይማርከው ያንን ባዩን ያን አሳዳጅ ጥበበኞችን ሊያሳፍር ያለምን ደካሞች መረጠ የከበሩትን ሊያሳፍር ምናምንቴዉን አከበረ ይሄው የዓለም ቤዛ ያለም ንጉስ ቤቴ ገባ ከእኔ ጋር እራት ሊቆርስ በረከቱን ሊያፈስስ ደካሞችን ሲጠራ ለእኔም ደርሶኛል ጥሪው ፈልጐ ከመረጠ ለምን አይባል ምርጫው ጥበበኞችን ሊያሳፍር ያለምን ደካሞች መረጠ የከበሩትን ሊያሳፍር ምናምንቴዉን አከበረ ጌታን ሳገለግል በምን ጥሩ ጐኔ እንዲህ ነው የምለው ታሪክ የለኝ እኔ መረጠኝ ወደደኝ ፈለገኝ መድህኔ እንዲሁ እንዲሁ ከነምኔ ከነምኔ (፫x)