ማንም ወንድሙን አይናቀው (2x) ያገኘም ያጣ ሰው ክቡር ነው (2x) ማንም ታናሹን አይናቀው (2x) ያገኘም ያጣ ሰው ክቡር ነው (2x) ለምን ተስፋ ይቁረጥ ለምንስ ይቆዝም ዳቦ አይሁንበት አይራበው ፍቅር ወንድሜ መገለሉ ይቅር (3x) ከእናቴም ባይወለድ የአዳም ዘር የእግዜር ፍጡር አብሬው ልቁረስ ልስጠው እኔ በልቼ አይራበው አያሳዝንም ወይ የራበው ሳያንሰው አያሳዝንም ወይ ፍቅር ሲቸግረው አያሳዝንም ወይ ጥግ ይዞ ሲያለቅስ አያሳዝንም ወይ አንጀቱ ሲላወስ መጽናናቱ (ልሁንለት ) እኔ እያለሁ (ወንድሜ አይሙት) ትላንትና (እንዴት ይረሳል) አፈር ባፈር (ላይ እንዴት ይኮራል) አያሳዝንም ወይ የራበው ሳያንሰው አያሳዝንም ወይ ፍቅር ሲቸግረው አያሳዝንም ወይ ጥግ ይዞ ሲያለቅስ አያሳዝንም ወይ አንጀቱ ሲላወስ መፅናናቱ (ልሁንለት) እኔ እያለሁ (ወንድሜ አይሙት) ትላንትና (እንዴት ይረሳል) አፈር ባፈር (ላይ እንዴት ይኮራል) ባልንጀራህን እንደራስህን ውደድ ለራስህ የክብር ወንበር አትውሰድ ጌታው ሲፈርድ ኋላ እንዳትወሰድ ባልንጀራህን እንደራስህን ውደድ ለራስህ ክብር ወንበር አትውሰድ (2x)