ዝም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው (3x) ዝም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው (3x) አዝ፦ ምሕረቱን አስቤ አቤት ስል ፍቅሩ አለ ለካ ፍቅሩን አስቤ አቤት ስል ባርኮቱ አለ ለካ አለ ለካ ታዲያ እንዴት አመስግኜው ልርካ (4x) አልጠፋብሽ ያለኝ ከልቤ ውስጥ የእግዚአብሔርስ ፍቅር አሳዳጊነቱ አባትነቱ ከህይወቴ ጀምር ትዝታ አይደለም እያነሳሁ ምተርክለት በርሱ አይደለም ወይ እስከ አሁኗ ድረስ ያለሁት (2x) የእግዚአብሔር ምህረት አቤት (3x) ሰው ወዳድነትህ አቤት (3x) የፍቅሩ ጥልቀት አቤት (3x) እሩህሩህነትህ አቤት አቤት አቤት (2x) አንድ ሁለት ብዬ ውለታውን አስቤ ልቆጥር ጥፍት ይለኛል ከየት ተነስቼ እንደምጀምር ይህ እንኳን ብረዳኝ ቢነግርልኝ ውስጤን ቢገልጸው እንደእግዚአብሔር ያለ የለም ብዬ ልደምድመው (2x) እንደእግዚአብሔር የለም አቤት (3x) ቢፈለግ ዘላለም አቤት (3x) እንደእሱ የለም አቤት (3x) ቢፈለግ ዘላለም አቤት አቤት አቤት (2x) አዝ፦ ምሕረቱን አስቤ አቤት ስል ፍቅሩ አለ ለካ ፍቅሩን አስቤ አቤት ስል ባርኮቱ አለ ለካ አለ ለካ ታዲያ እንዴት አመስግኜው ልርካ (4x)