Song Lyrics

እግዚአብሔር ፍቅር ነው

ያ ሰነፍ ቢመስለው ያወቀ ከአባቱ እቅፍ ወጥቶ ወደቀ ሄደና እንዳሻው እንደልቡ እስኪረዳ እንደጣለ ክብሩን ተመልሶ መጣ በሀዘን ብሎ እንደባሪያው እንኳ ብሆን መመለሱን ያየም አባቱ አቀፈው ልክ እንደበፊቱ አዝ፦ ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ኧረ ያሳየ የተገበረ (2x) ይቺ ሴት ኃጢአተኛ ናት ህግ አለህ አንተም ፍረድባት እያሉ ላመጧት ለዚያች ነፍስ ጠበቁ ምን እንደሚመልስ እርሱ ግን እውነቱን ተናገረ ሁሉም ራሱን እንዲያይ አረገ የእሷንም ፍርዷን አንስቶላት አትድገሚው ልጄ ሂጂ አላት አዝ፦ ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ኧረ ያሳየ የተገበረ (2x) ሁሉ እንዲድን አንዷ እንዳትጠፋ ቢገደው ያ መልካም እረኛ በረት ያሉትን ይተውና ይሄዳል እሷኑ ፍለጋ ያሰማታል ድምጹን አውጥቶ በእቅፉ ሊያስገባት ጓጉቶ ነፍሱን ስለበጐቹ ያኖረው እውነተኛ ፍቅር እርሱ ነው አዝ፦ ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ኧረ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ኧረ ያሳየ የተገበረ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection