Song Lyrics

አለኝ አባት

ሚያስፈልገኝን ያረገልኝ ተንከባክቦ የሚያሳድገኝ የሚሸከመኝ እንደልጅነቴ አለልኝ ቸሩ አባቴ (2x) አዝ፦ አለኝ አባት አባት የምመካበት አባት አለኝ አባት አባት ማስፈራራበት አባት ጠላቴ ሆይ ስማ ወዴት ወዴት አትዘንጋው እንጂ አንዳለኝ አባት እንደ አይን ብሌን ምያስብ ምጠነቀቅ በልጁ የመጣበትን የማይምር የማይለቅ አዝ፦ አለኝ አባት አባት የምመካበት አባት አለኝ አባት አባት ማስፈራራበት አባት እግዚአብሔር አባቴ እኩያ የለውም ግን እኮ ማንንም አይንቅም (2x) ይቅርታው ብዙ ሁልጊዜ የሚምር መልካሙን መንገድ የሚያስተምር ማማክረው የሚመክረኝ አባቴ እያለ ምን አባዘነኝ ሰውን ተስፋ ማድረጉ በቃኝ በቃኝ ግራ ቀኝ ማየቱ በቃኝ በቃኝ ጉዳይ አለኝ ከአንተ ጋ መጥቻለሁ ላወጋ ጉዳይ አለኝ ከአንተ ጋ መጥቻለሁ ላወጋ መጥቼም ሸክሜን አራግፈለሁ ጌታ እንደማትሰለቸኝ ተማምኛለሁ ጌታ ሁልጊዜ የፍቅር ብሩህ ፊት አለህ ጌታ የሚያቀርብ የሚያስጠጋ ጌታ ጉዳይ አለኝ ከአንተ ጋ መጥቻለሁ ላወጋ ጉዳይ አለኝ ከአንተ ጋ መጥቻለሁ ላወጋ ከአንተ ጋር ልቆራኝ ከአንተ ጋር ልወዳጅ ይሄ ነው የሚረባ ይሄ ነው የሚበጅ (4x) ጉዳይ አለኝ ከአንተ ጋ መጥቻለሁ ላወጋ ጉዳይ አለኝ ከአንተ ጋ መጥቻለሁ ላወጋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection