አዝ፦ በከንቱ እንዳለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ የሕይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ (2x) ያየሁትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ (2x) እንደሄድኩም አልቀር ዕረፍቴ እገባለሁ እገባለሁ (2x) ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ ወደ ዕረፍቴ ወደ አገሬ እገባለሁ ወደ አገሬ (2x) ተስተጓጉዬ እንዳልቀር ሜዳ ላይ የፊቴን ትቼ ግራና ቀኝ ሳይ አሳይቶኛል አልፎበት መንገዱን እከተላለሁ የርሱን ፍለጋውን መንገዴ ነው የሱስ እውነት ሕይወት ቀና ምሄድበት አብ ጋር ምደርስበት (4x) አዝ፦ በከንቱ እንዳለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ የሕይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ (2x) ያየሁትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ (2x) እንደሄድኩም አልቀር ዕረፍቴ እገባለሁ እገባለሁ (2x) ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ ወደ ዕረፍቴ ወደ አገሬ እገባለሁ ወደ አገሬ (2x) ሰፊው ጐዳና አማራጭ ስላለው አልመኘውም ዳርቻው የሞት ነው በጠባቡና በሕይወት መንገድ ላይ እራመዳለሁ ተስፋይቷን እንዳይ መንገዴ ነው የሱስ እውነት ሕይወት ቀና ምሄድበት አብ ጋር ምደርስበት (4x) አዝ፦ በከንቱ እንዳለፋ ስለራራልኝ ስላዘነልኝ የሕይወትን መንገድ አቅጣጫ አሳየኝ (2x) ያየሁትን መንገድ ይዤ እዘልቃለሁ (2x) እንደሄድኩም አልቀር ዕረፍቴ እገባለሁ እገባለሁ (2x) ወደ ዕረፍቴ እገባለሁ ወደ ዕረፍቴ ወደ አገሬ እገባለሁ ወደ አገሬ (2x)