አዝ፦ አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ ሲገለጥ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ ሲታይ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ የኑሮዬ ለሊት እንዲነጋ የማውቅበት የሕይወቴ ለሊት ማዳኑን የማይበት (2x) ዝም ባለው በድቅድቅ ለሊት አጋዥ በሚያሻበት ግራ ቀኝ እያየሁ ስጣራ ፈልጌ እረዳት አምላኬ መንፈሴን አንቅቶ አበራልኝ እውነቱን በከበበኝ ጨለማ መሃል አሳየኝ ምሕረቱን በሰማይ ያሉ ከዋክብት ሲመሽ እንደሚደምቁት ዙሪያዬ ሲጨልምብኝ የአምላኬን ማዳን አየሁት (2x) አዝ፦ አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ ሲገለጥ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ አቤት ውበቱ አቤት ውበቱ የለሊቱ ሲታይ እውነቱ ውበት አለው ለሊቱ የኑሮዬ ለሊት እንዲነጋ የማውቅበት የሕይወቴ ለሊት ማዳኑን የማይበት (2x) ሊያባብለኝ በምድረበዳ ወሰደኝ አስተምሮ አስተካክሎ ሊቀርፀኝ በውዴ ላይ በርሱ ብቻ ተደግፌ ይህች ማን ናት የሚሉኝን እንዳይ አልፌ ያለኝን በሙሉ ወዲያ ማዶ አሻገረው ብቻዬን ሊያይ ወዶ ሲታገለኝ ቆየ በጨለማው አስቸጋሪው ልቤን እስክረታው (2x) ሥሜን ሊቀይር አድኖም ሊያስቀረኝ የሁለት ክፍል ሰራዊት ሊያረገኝ ሥርዓቱን እማር ዘንድ አስጨነቀኝ (4x)