አይናፍቀኝም ሃገሩ ያ ጨለማ ያ ሃሩሩ ነፃ አውጥቶኛል ጌታዬ በነፃነት ልኖር እፎይ ብዬ (2x) አራገፈና ሸክሜን ያጎበጠኝን ቀንበሬን አሸክሞኛል የራሱን የቀለለ የለዘበውን አሸክሞኛል ፍቅሩን እየገለፀ ትርጉሙን አሸክሞናል ፀጋውን እንደመሰክር ስራውን አዝ፦ እገዛለታለሁ በደስታ አሸንፎኛል ይሄ ጌታ በሰው ፍቅር የወደቀ እንኳን ይሰጥ የለ ወይ እራሱን ኧኸይ በፍቅሩ ገመድ ኧኸይ ተጠፍሬያለሁ ኧኸይ ውሎ አያድርም አያይ አያይ ልቤን እረታው ሁለት ጌቶች አይገዙኝም ጉዳዬ ሌላ አልደብልም እግዚአብሔር ስላለው ብልጫ አያዳግትም ለምርጫ እግዚአብሔር ስላለው ብልጫ አያስቸግርም ለምርጫ እግዚአብሔር ስላለው ብልጫ አያዳግትም ለምርጫ አዝ፦ እገዛለታለሁ በደስታ አሸንፎኛል ይሄ ጌታ በሰው ፍቅር የወደቀ እንኳን ይሰጥ የለ ወይ እራሱን ኧኸይ በፍቅሩ ገመድ ኧኸይ ተጠፍሬያለሁ ኧኸይ ውሎ አያድርም አያይ አያይ ልቤን እረታው ዝም ብዬ እንዴት እኖራለሁ ላገኘሁት እጄን እያነሳሁ አልሟገትም እያልኩ ምን አለበት የእግዚአብሔር ፍቃድ ያልሆነ እሱ ሞት አለበት አልቀጥፈውም እጄን ሰድጄ ዛሬ የሚያጠፋ የምገለውን የሞት ፍሬ ይቅርብኝ እንጂ ከንቱ ከንቱ ጨዋታ አሳስቆ ይለይ የለ ወይ ከውዱ ጌታ (2x) ዝም ብዬ እንዴት እኖራለሁ ላገኘሁት እጄን እያነሳሁ አልሟገትም እያልኩ ምን አለበት የእግዚአብሔር ፍቃድ ያልሆነ እሱ ሞት አለበት አልቀጥፈውም እጄን ሰድጄ ዛሬ የሚያጠፋ የምገለውን የሞት ፍሬ ይቅርብኝ እንጂ ከንቱ ከንቱ ጨዋታ አሳስቆ ይለይ የለ ወይ ከውዱ ጌታ (2x) አይናፍቀኝም ሃገሩ ያ ጨለማ ያ ሃሩሩ ነፃ አውጥቶኛል ጌታዬ በነፃነት ልኖር እፎይ ብዬ (2x)