Song Lyrics

እግዚአብሔር አለ

የጭንቁ ጊዜ ሳይመጣ ግዳጅ ሳይሆንብኝ አመልካለሁ በውዴታ አየተገዛሁ ለጌታ (2x) ግዴታዬን ለማክበር አይደለም የማመሰግነው ይልቁንም ፍቅሩ ጨምሮብኝ አጣሁኝ የምለው (2x) ሳይወዱ ጌታ ነህ ቢሉት ቀን አስገድዷቸው እኔ አስቲ ልዘምርለት ምቹ ሳለ ጊዜው (2x) ስንት የምለው ነገር በልቤ የለኝ ቃላት አቅም አጣ ተቸገርኩ እያነሰብኝ እኔ ከማቀርበው እልፍ የምስጋና ቃል የእግዚአብሔር የአንድ ቀን ምሕረቱ ይመዝንብኛል የሚያሳስበኝ እሱን አንዴት እንደማከብር ነው የሚያሳስበኝ እሱን አንዴት እንደማስከብር ነው የሚያሳስበኝ ጌታን አንዴት እንደማከብር ነው የሚያሳስበኝ እሱን አንዴት እንደማስከብር ነው ነገር ጐደለ እግዚአብሔር አለ ኑሮም ጐደለ እግዚአብሔር አለ (2x) አንዳንድ ጊዜ አይደለም የማመሰግነው ሲጐልም እሰየሁ ሲሞላም እሰየሁ የማመሰግንበት ምክንያቴ የእግዚአብሔር ነው (2x) ጌታ ካለ ቤቴ ሙሉ ነው (2x) እጠግባለሁ ፊቱን እያየሁ (2x) እሱ ካለ ቤቴ ሙሉ ነው (2x) እጠግባለሁ ፊቱን እያየሁ (2x) የሚያሳስበኝ አንተን አንዴት እንደማከብር ነው የሚያሳስበኝ አንተን አንዴት እንደማስከብር ነው (2x) አፌን ሞልቼ እንድዘምረው የሚጋብዘኝ ማንነትህ ነው (2x) ለማንነትህ ክብር ይድረስህ ለማንነትህ ክብር ይሁንልህ ለማንነትህ ክብር ይኸውልህ ለማንነትህ ክብር ይሁንልህ ነገር ጐደለ እግዚአብሔር አለ ኑሮም ጐደለ እግዚአብሔር አለ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection