የሆነው ነገር እርሱ የሚሆን ነው አሃ የተደረገው እርሱ የሚደረግ ነው አሃ (2x) ከፀሃይ በታች ኣዲስ ነገር የለም እግዚአብሔር ብቻ አይለመድም (2x) ሰው በእውቀቱ ላይ ደርቦ እውቀትን ቢጨምር ይህም ከንቱ ነው ከንቱ ለዓይኑ ያማረውን ከማድረግ ነፍሱን ባይከለክል ይህም ከንቱ ነው ከንቱ ማረፍያዬ ብሎ ቤቶቹን ቢያሳምር ቢያስጌጥ ይህም ከንቱ ነው ከንቱ ብርና ወርቅን አከማችቶ ለነገው ቢያስቀምጥ ይህም ከንቱ ነው ከንቱ አዝ፦ ለሰው ከድካሙ በቀር ትርፉ ምንድን ነው ይልቅ በጉብዝናው ወራት ጌታን ማሰብ ነው (2x) ሳይደክሙ ጌታን ማሰብ ነው ሳይጨልም ጌታን ማሰብ ነው በሩ ሳይዘጋ ጌታን ማሰብ ነው ነፍስም ሳትወጣ ጌታን ማሰብ ነው አይ ጐበዝ የተባለው ሰውአገር ሁሉ የሚያደንቀው ጥሮ ግሮ ያከማቸውን ጥሎት ሄደ ሳይበላው ሃብቱን ይሄም ከንቱ መድረሻው ምንድን ነው እድሜውን ሁሉ ጠፍሮት ስንፍናው እንደተባለ እንደቀረም መና እሱም ሄደ ሞት ቀደመውና ሳይደክሙ ጌታን ማሰብ ነው ሳይጨልም ጌታን ማሰብ ነው በሩ ሳይዘጋ ጌታን ማሰብ ነው ነፍስም ሳትወጣ ጌታን ማሰብ ነው አዝ፦ ለሰው ከድካሙ በቀር ትርፉ ምንድን ነው ይልቅ በጉብዝናው ወራት ጌታን ማሰብ ነው (2x)