Song Lyrics

በየማለዳው

Bethlehem Tezera
Edimeye Bebetih Yilek
ስለ ዛሬ የምን ታውቂያለሽ ቢሉኝ አንድ ነገር አንድ መልስ አለኝ በእውነት በእርግጠኛነት አለ የእግዚአብሔር ቸርነት ስለ ነገስ ምን ታውቂያለሽ ቢሉኝ አንድ ነገር አንድ ዕውቀት አለኝ በእውነት በእርግጠኛነት አለ የእግዚአብሔር ቸርነት በየማለዳው የምረዳው ዕለት በዕለት የሚታይ እውነት (2x) እንደ እግዚአብሔር ያለ እንደ ሌለ እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ (2x) ቸር ባይሆን ባለ ምህረት እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (2x) ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑት ለሚወዱትም ቸር ለሚያምኑበት (2x) ያለጠፋሁት በምን ምክኒያት ከቦኝ እንጂ የአንተ ምህረት እያለፈ እየተከተለኝ ክፉዉን ሁሉ ጥግ አስያዘልኝ የደረስክለት ያውራ እስኪ ያውራ ደግነትህን ይመስክር በአንተ የቀናለት አሃ ሕይወቱ መስመር (2x) አልጣለኝም ደጋግ እጆችህ ፍቅር ናቸው ዛሬም ዓይኖችህ ለዘለዓለም ቤትህ እኖራለሁ ወደኸኛል እስከ መጨረሻው የደረስክለት ያውራ እስኪ ያውራ ደግነትህን ይመስክር በአንተ የቀናለት አሃ የሕይወቱ መስመር (2x) ስለ ዛሬ የምን ታውቂያለሽ ቢሉኝ አንድ ነገር አንድ መልስ አለኝ በእውነት በእርግጠኛነት አለ የእግዚአብሔር ቸርነት ስለ ነገስ ምን ታውቂያለሽ ቢሉኝ አንድ ነገር አንድ ዕውቀት አለኝ በእውነት በእርግጠኛነት አለ የእግዚአብሔር ቸርነት በየማለዳው የምረዳው ዕለት በዕለት የሚታይ እውነት (2x) እንደ እግዚአብሔር ያለ እንደ ሌለ እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ (2x) ቸር ባይሆን ባለ ምህረት እኔ/አንዷ ነበርኩ ከሚጠፉት (2x) ለክፉዎችም ቸር ለማያመሰግኑት ለሚወዱትም ቸር ለሚያምኑበት (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection