Song Lyrics

የሰላም ትጉ

Bethlehem Tezera
Edimeye Bebetih Yilek
አዝ፦ ሰው በምን ይረካል ልቡ ዓለሙም አያልፍም ልኩ ጌታ ነው የሰላም ጥጉ (2x) ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ (2x) ልብህ ሲፈካ እንደ አበባ በአገኘው ነገር ሲፀናና ደግሞ በዚያው ልክ የሀዘን ድባብ ድብት ሲያደርገው ተስፋ ሲቆርጥ ስንቱ ይታያል በሕይወት ለዚያች ዕድሜ ተችሮት ግን አዋቂ ያ ብልሁ በአምላክ ሲሆን ነው መደሰቱ የማይናወጥ ሰላሜን ደስታዬን እኔ አግኝቻለሁ ኢየሱስ ጌታዬን የምድር ስኬት ሚሰጠው ምንድን ነው ከኢየሱስ ሌላ ደስታ አለ ባይ ማን ነው አዝ፦ ሰው በምን ይረካል ልቡ ዓለሙም አያልፍም ልኩ ጌታ ነው የሰላም ጥጉ (2x) ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ (2x) መች በአንድ ነገር ልብ ይረካል አንዱ ሲሰጠው ሌላ ይሻል ያሻውንም ቢያገኝ ሰው ምኞቱ በቃ አይልም አይሞላለት ቋቱ ሕይወት የሚረጋው በእረፍት ኢየሱስ ሲገባ ወደ ቤት የሰላም ምንጩን ከተጠጉ ሌላ ደስታ አይፈልጉ የማይናወጥ ሰላሜን ደስታዬን እኔ አግኝቻለሁ ኢየሱስ ጌታዬን የምድር ስኬት ሚሰጠው ምንድን ነው ከኢየሱስ ሌላ ደስታ አለ ባይ ማን ነው (2x) አዝ፦ ሰው በምን ይረካል ልቡ ዓለሙም አያልፍም ልኩ ጌታ ነው የሰላም ጥጉ (2x) ኢየሱስ ነው የደስታ ጥጉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection