አዝ፦ አንደበቱን የሚገታ ሰውነቱን ይገዛልና ለአፍህ ጠባቂ አኑር የሕይወት ቃል መውጫ በር ናትና ዘሯም ሲያፈራ እጥፍ ነውና ለአፍህ ጠባቂ አኑር አንደበቱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታልና ለአፍህ ጠባቂ አኑር የሕይወት ቃል መውጫ በር ናትና ዘሯም ሲያፈራ እጥፍ ነውና ለአፍህ ጠባቂ አኑር አመጸኛ አለ ሙሉ ሥጋውን ያሳድፋል ትንሽ እዓት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያጋያል ከአንድ ምንጭ መራርና ጣፋጭ እንዳይቀዳ ከአንደበትህ አንዴ መርገም አንዴ ባርኮት አይውጣ ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት መልካም ፍሬ ሚለቀምባት የጠቢብ ቃል እንደምንጭ ነው የተፍገመገመውን የሚያቀናው (2x) አዝ፦ አንደበቱን የሚገታ ሰውነቱን ይገዛልና ለአፍህ ጠባቂ አኑር የሕይወት ቃል መውጫ በር ናትና ዘሯም ሲያፈራ እጥፍ ነውና ለአፍህ ጠባቂ አኑር አንደበቱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታልና ለአፍህ ጠባቂ አኑር የሕይወት ቃል መውጫ በር ናትና ዘሯም ሲያፈራ እጥፍ ነውና ለአፍህ ጠባቂ አኑር መልካም ዘመን ማየት ካሻህ አፍህን ከክፉ ከልክል በቃል ብዛት ኃጢአት ሳይኖር አይቀርምና አስተውል ልብ የሞላውን ያንኑ አፍ ይናገራልና ጆሮህን ለትምህርት አቅና ጥበብ ልብህን ይሙላ ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ናት መልካም ፍሬ ሚለቀምባት የጠቢብ ቃል እንደምንጭ ነው የተፍገመገመውን የሚያቀናው (2x) አዝ፦ አንደበቱን የሚገታ ሰውነቱን ይገዛልና ለአፍህ ጠባቂ አኑር የሕይወት ቃል መውጫ በር ናትና ዘሯም ሲያፈራ እጥፍ ነውና ለአፍህ ጠባቂ አኑር አንደበቱን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃታልና ለአፍህ ጠባቂ አኑር የሕይወት ቃል መውጫ በር ናትና ዘሯም ሲያፈራ እጥፍ ነውና ለአፍህ ጠባቂ አኑር