Song Lyrics

ወዴት አለህ

Bethlehem Tezera
Edimeye Bebetih Yilek
ልቤ ዋተተ ዋተተ መንፈሴም ታወከብኝ ልጄ አንተን አጥቼ ከጉያዬ እንዴት ልረፍ በምን . (1) . እህ እህህህህ እህህ ሆነብኝ ጠዋት ማታ ወንድሞችህ ቢኖሩም በቤት አይተኩትም ለአንተ ያለኝን ቦታ አዝ፦ ወዴት አለህ ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (2x) ደጅ/በር አፍ ላይ ቆሞ ያንኳኳል ወዳጅ ይጣራል ወዳጅ (2x) ድምጹን ሲያሰማ አስገባው ከፍተህ አይጥና ደጅ አይጥና ደጅ (2x) እናት ትረሳ ይሆናል አምጣ የወለደችውን እኔማ እንዴት እንዴት ነው እንዴት አንተን ጥሎ መኖር በሞቀ ቤት ልጄን ካልያዝኩት አልረካ ክርትት አለ ዓይኔ አንተን ፍለጋ ወድሃለሁ ልጄ ናና ናና ሙሉ እንዲሆን የቤቴ ምሥጋና አዝ፦ ወዴት አለህ ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (2x) ደጅ/በር አፍ ላይ ቆሞ ያንኳኳል ወዳጅ ይጣራል ወዳጅ (2x) ድምጹን ሲያሰማ አስገባው ከፍተህ አይጥና ደጅ አይጥና ደጅ (2x) አባ አባባ ስትለኝ እስቲ ልስማህ ያ ድምጽህ ናፈቀኝ ሸክምህን አውርድ ከጫንቃህ ላሳርፍህ አለሁ አባትህ የሚያሳየው ጐልጐታ ዛሬም ያው ነው ፍቅሬ መች ተገታ በላ እንሂድ ወደ ቤታችን እኔም ልረፍ አግኝቼ አንተን አዝ፦ ወዴት አለህ ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (ወዴት አለህ) ወዴት አለህ (ድምጼን ሰምተህ) ድምጼን ሰምተህ አለሁ በለኛ (አለሁ በለኛ) ፈጠን ብለህ ወደ እቅፌ ግባ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection