ሞገስ የጠገበ ክብር የተረፈው ምሥጋና አምልኮ ገንዘቡ የሆነው እርሱማ የእኔ ጌታ ነው እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (2x) ሰማይ ምድሩ የተገረመበት ለውበቱ የተነገረለት እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (2x) ክብሩ ሰማያትን የከደነ ምሥጋናው በምድር የተመመ እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (2x) የጌታዎች ጌታ የነገሥታት ጌታ የኃያላን ጌታ የአለቆች ጌታ የመሪዎች ጌታ የብርቱዎች ጌታ (2x) እግዚአብሔር እግዚአብሔር የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (2x) የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (2x) አዶናይ ፀባዖት ኤልካዶሽ የሆነው ራሱን ተማምኖ አውቆ እኔ ነኝ ያለው እርሱማ የእኔ ጌታ ነው እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (2x) ሰማያትን በስንዝር የለካ ዓለማትን በእጆቹ የያዘው እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (2x) ከዋክብትን በሥም የሚጠራ በቀን በሌት ሁሉን የሚያሰማራ እርሱማ የእኔ ጌታ ነው (2x) የጌታዎች ጌታ የነገሥታት ጌታ የኃያላን ጌታ የአለቆች ጌታ የመሪዎች ጌታ የብርቱዎች ጌታ (2x) እግዚአብሔር እግዚአብሔር የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (2x) የእኔ አምላክ ነው እርሱማ እግዚአብሔር (2x)