አልዋሽህም ልቤን ታያለህና አልዋሽህም የልብ አምላክ ነህ እላለሁ እርቦኛል በእውነት ፊትህ . (1) . ላምልክህ ይርዳኝና መንፈስህ ከስሬ ደርቼ ድሪቶዬን ከላይ ብለብሰው የፀዳውን ሰው እንደው የሚያየው ፊቴ ፊቴን እከልላለሁ ገበናዬን (2x) ግን አንተ አትዋሽም አትታለል ዓይንህ ዘልቆ ልብን ያያል ዓይንህ ዘልቆ ልብን ያያል (2x) የቀድሞውን ፍቅር አጣሁት ፈላልጌ ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ወዴት ነው ማደጊያዬ ኧረ እኔስ ፈራሁኝ ወዴት ነው . (2) . እግዚአብሔር ደጅ እንዳልጠናሁኝ ዛሬማ ላፍታ እንኳ አቅም አጣሁ (2x) ናፈቀኝ የጥንቱ ክብር ናፈቀኝ ቤቴ የነበረ ናፈቀኝ ኦ እግዚአብሔር ናፈቀኝ ረሃቤ ትጋቴ ናፈቀኝ ትንሿ አንዷ ሀሳቤ ናፈቀኝ ያ ፀሎቴ የተገለጠው ማንነቴ ይኸው በፊትህ መድኃኒቴ አቅም አጣሁኝ አግዘኝ ያዘኝ ኃይልህን አልብሰኝ (2x) ለአንተ ያለኝ ፍቅር ትኩስ የማይበርድ በልቤ የሚኖር ሁል ጊዜ የሚነድ (2x) መስሎኝ እንዳልነበር በልጅነቴ ወራት ራሴን አገኘሁት ልምድ ሆኖብኝ ቀላት ቤቴን አዘረፍኩት ከፍቼ ለጠላት ናፈቀኝ ለቃልህ ያለኝ ቦታ ናፈቀኝ ያንን የእሺታ ናፈቀኝ ኦ እርዳኝ ጌታ ናፈቀኝ ለአንተ ያለኝ ክብር ናፈቀኝ ሥምህ ሲነገር ናፈቀኝ ኦ እግዚአብሔር የተገለጠው ማንነቴ ይኸው በፊትህ መድኃኒቴ አቅም አጣሁኝ አግዘኝ ያዘኝ ኃይልህን አልብሰኝ (2x) ድልደላ/. (4) . ይቅርብኝ ልመልስ ወደ ልብህ ወደ ሀሳብህ ልድረስ ልሸከመው የመስቀልህን ፍቅር ተመልሼ ወደ ኋላ አልመልከት አድስልኝ የቀድሞውን . (3) . ናፍቆት ሆኖ ምኞት ሆኖ እንዳይቀር ሰምቼ አንተን እንዳፈራበት ለም አድርገው የልቤን መሬት (2x)