ቤትን ሊሰራ የተመረጠው የተወደደ ጥበብ የሞላው (2x) ክብር ሲሆንልት ዝና ሲተርፈው የአባቶቹን አምላክ እንደማያውቀው ጣዖት አምልኮ ሞት ሆነ ፍጻሜው አዝ፦ ዕድሜዬ ይለቅልኝ ቤትህ ይለቅልኝ በቤትህ ሕይወቴ ይመርልኝ ፊትህ ይመርልኝ በፊትህ ሩጫዬ እንዳይገታ ጠብቀኛ የእኔ ጌታ እኔ እንዳልሆን ለእኔው ጠላቴ ሰውረኝ ከዓይን አምሮቴ (2x) አህያ ፍለጋ ተልኮ ቢወጣ እጣ ወደቀበት ህዝብን እንዲመራ ከፍልስጤማዊ ነጻ እንዲያወጣ ደርሶ ንጉሥ ሲሆን ትህትና አጣ ክፉ መንፈስ ያዘው ከአንተ መንገድ ወጣ መውደቂያው ሆነበት ኤልቡአ ተራራ አዝ፦ ዘመኔ ይለቅልኝ ቤትህ ይለቅልኝ በቤትህ ሕይወቴ ይመርልኝ ፊትህ ይመርልኝ በፊትህ ሩጫዬ እንዳይገታ ጠብቀኛ የእኔ ጌታ እኔ እንዳልሆን ለእኔው ጠላቴ ሰውረኝ ከዓይን አምሮቴ (2x) በትንሳኤው ጉልበት ዓይናቸው የበራ ጨከኑ በሕይወት ለሰሙት አደራ ቤታቸውን ሰጡ ለወንጌል አደራ አርበኞች ሆነዋል እስሩም ቢጠና ነገሥታት ፊት ቆሙ ወንጌልን ሰበኩና ሰማእት ሆነው አለፉ ዋጋ ተመኑና ድል ለነሳው ከሕይወት አክሊል ታቀዳጃለህ ድል ለነሳው በቤትህ እንዲኖር ትሾመዋለህ ጅማሬዬ እንዳማረልኝ ፍጻሜዬም ይስመርልኝ መዝገብ ላከማች በሠማይ ቤትህ ብል በማይበላው በሌለበት ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዕድሜዬ ይልቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዘመኔ ይልቅ እቤትህ (2x) ድል ለነሳው ከሕይወት አክሊል ታቀዳጃለህ ድል ለነሳው በቤትህ እንዲኖር ትሾመዋለህ ጅማሬዬ እንዳማረልኝ ፍጻሜዬም ይስመርልኝ መዝገብ ላከማች በሠማይ ቤትህ ብል በማይበላው በሌለበት ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዕድሜዬ ይልቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዘመኔ ይልቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ሕይወቴ ይመር እፊትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ወበቴ ይልቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዕድሜዬ ይልቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዘመኔ ይልቅ እቤትህ