Song Lyrics

ዕድሜዬ በቤትህ ይለቅ

Edmiye Bebetih Yileq

Bethlehem Tezera
Edimeye Bebetih Yilek
ቤትህን ሊሰራ የተመረጠው የተወደደ ጥበብ የሞላው (፪x) ክብር ሲሆንለት ዝና ሲተርፈው የአባቶቹን አምላክ እንደማያውቀው ጣዖት አምልኮ ሞት ሆነ ፍጻሜው አዝ፦ ዕድሜዬ ይለቅልኝ ቤትህ ይለቅልኝ በፊትህ ሕይወቴ ይመርልኝ ፊትህ ይመርልኝ በፊትህ ሩጫዬ እንዳይገታ ጠብቀኛ የእኔ ጌታ እኔ እንዳልሆን ለእኔው ጠላቴ ሰውረኝ ከዓይን አምሮቴ (፪x) አህያ ፍለጋ ተልኮ ቢወጣ እጣ ወደቀበት ህዝብን እንዲመራ ከፍልስጤማዊ ነጻ እንዲያወጣ ደርሶ ንጉሥ ሲሆን ትህትና አጣ ክፉ መንፈስ ያዘው ከአንተ መንገድ ወጣ መውደቂያው ሆነበት የጊልቦዓ ተራራ አዝ፦ ዘመኔ ይለቅልኝ ቤትህ ይለቅልኝ በፊትህ ሕይወቴ ይመርልኝ ፊትህ ይመርልኝ በፊትህ ሩጫዬ እንዳይገታ ጠብቀኛ የእኔ ጌታ እኔ እንዳልሆን ለእኔው ጠላቴ ሰውረኝ ከዓይን አምሮቴ (፪x) በትንሳኤው ጉልበት ዓይናቸው የበራ ጨከኑ በሕይወት ለሰሙት አደራ ቤታቸውን ሰጡ ለወንጌል አደራ አርበኞች ሆነዋል እስሩም ቢጠና ነገሥታት ፊት ቆሙ ወንጌልን ሰበኩና ሰማዕትሆነው አለፉ ዋጋ ተመኑና ድል ለነሳው ከሕይወት አክሊል ታቀዳጃለህ ድል ለነሳው በቤትህ እንዲኖር ትሾመዋለህ ጅማሬዬ እንዳማረልኝ ፍጻሜዬም ይስመርልኝ መዝገብ ላከማች በሠማይ ቤትህ ብል በማይበላው በሌለበት ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዕድሜዬ ይለቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዘመኔ ይለቅ እቤትህ (፪x) ድል ለነሳው ከሕይወት አክሊል ታቀዳጃለህ ድል ለነሳው በቤትህ እንዲኖር ትሾመዋለህ ጅማሬዬ እንዳማረልኝ ፍጻሜዬም ይስመርልኝ መዝገብ ላከማች በሠማይ ቤትህ ብል በማይበላው በሌለበት ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዕድሜዬ ይለቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዘመኔ ይለቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ሕይወቴ ይመር እፊትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ውበቴ ይለቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዕድሜዬ ይለቅ እቤትህ ሳታፍርብኝ እንድቆም ፊትህ ዘመኔ ይለቅ እቤትህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection