Song Lyrics

የሕይወት እንጀራ

Bethlehem Tezera
Abet Amilake
አንተ የሕይወት እንጀራ ነህ አንተ የሕይወት ብርሃን (2x) ታጠግባለህ ታረካለህ ታጠግባለህ ታረካለህ (2x) ከአንተ ወዴት ወዴት እሄዳለሁ ወዴት እሄዳለሁ (2x) ተስፋዬ ነህ አንተን እጠጋለሁ (2x) አምላኬ ነህ አንተን እጠጋለሁ የሙጥኝ ይዣለሁ ያንን ትቼ ይህንን ትቼ አንተን ላመልክህ መጥቻለሁ (2x) ለአንተ ለመኖር መጥቻለሁ አንተን ላመልክህ መጥቻለሁ ያንን ትቼ ይህንን ትቼ ላገለግልህ መጥቻለሁ ለአንተ ለመኖር መጥቻለሁ አንተን ላከብርህ መጥቻለሁ አንተን ላመልክህ መጥቻለሁ አማራጬ/አባቴ አይደለህ ብቸኛ መንገዴ ነህ ብቸኛ መንገዴ ነህ (2x) ያለ አንተማ እንዴት ሊሆንልኝ ያለ አንተማ ምንም አያምርብኝ ያለ አንተማ ሁሉም ከንቱ ነው ያለ አንተማ ኑሮም ትርጉም ይለው ያለ አንተማ መውጣት መግባት የለም ያለ አንተማ መንገዱም አይቀና ያለ አንተማ እንዲያው መቅበዝበዝ ነው ያለ አንተማ መና መቅረት ነው ታዲያ ከአንተ ወዴት ወደ ማን ትውት/እርግፍ አድርጊያለሁ ሌላውን (2x) ትዝታም የለኝም ትውስታም የለኝም ከተውቁት/ካልሆንኩት ውስጥ አንዱም አይቆጨኝም (2x) አንተን አይቶ ልቤ አረፈልኝ እዚህም እዚያም ማለት ቀረልኝ (2x) ታዲያ ከአንተ ወዴት ወደ ማን ትውት አድርጊያለሁ ሌላውን ታዴያ ከአንተ ወዴት ወደ ማን ኦሆ እርግፍ አድርጊያለሁ ሌላውን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection