Song Lyrics

ጌታ አሰራሩ

Bethlehem Tezera
Abet Amilake
ጌታ አሰራሩ ልዩ ልዩ ነው (2x) ምን ትሰራለህስ ማነው የሚለው (2x) ጌታ አሰራሩ ልዩ ልዩ ነው (2x) ምን ታደርጋለህስ ማነው የሚለው (2x) እግዚአብሔር እርሱ ትልቅ የሚሰራውን የሚያውቅ አምላኬ እርሱ ትልቅ የሚያደርገውን የሚያውቅ ለእኔም እርሱ ካለልኝ ለምን እሰጋለሁኝ ለእኔም እርሱ ካለልኝ ለምን አስባለሁ ለእኔም እርሱ ካለልኝ ማመስገን ነው ያለብኝ ማንም ከርሱ ጋራ ቢሟገትም ከሺህ ነገር እንዱን አይመልስም እንዲህና እንደዚያ ማን ይለዋል አደራረጉ ግን አፍ ያስይዛል እግዚአብሔር እርሱ ትልቅ የሚሰራውን የሚያውቅ አምላኬ እርሱ ትልቅ የሚያደርገውን የሚያውቅ ማንንም አይፈልግ አስተማሪ ሁልን የሚያደርገው ያላማካሪ ብቻውን ተዓምር ድንቅ ይሰራል በዛ ሲጠበቅ በዚህ ይመጣል አማካሪ የሌለው ንጉሥ የእኔ ኢየሱስ አስተማሪ የሌለው መሪ የእኔ ጌታ (2x) ይሄኛው ልክ አይደለም አስተካክለው ይህንን አይባልም እኔ አሳይሃለሁ በዚህ መንገድ ሂድልኝ አይባልም (2x) አይባልም (4x) እግዚአብሔር እርሱ ትልቅ የሚሰራውን የሚያውቅ አምላኬ እርሱ ትልቅ የሚያደርገውን የሚያውቅ ምድርን አደራ የሰጠው ማነው ዓለምን ያዝልኝ ያለው ማነው አገዛዝን ያስተማረው ማነው (2x) ሁሉ የርሱ አይደለም ወይ አይደል ወይ የለበትም አስተዳዳሪ የበላይ (2x) አማካሪ የሌለው ንጉሥ የእኔ ኢየሱስ አስተማሪ የሌለው መሪ የእኔ ጌታ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection