Song Lyrics

ምትክ የለህ

Bethlehem Tezera
Abet Amilake
እንደ እናት ነህ አልልም እንደ አባት ነህ አልልም ምትክ የለህ መድህኔ አንድ እኮ ነህ ለእኔ (2x) አንድ ነህ ለእኔ ጌታ የለኝም የማቆመው/የምተካው በአንተ ቦታ (2x) አንዱ ሲመጣ አንዱ ይሄዳል በምድር ያለው ይቀያየራል ኢየሱሴ ካንተ የተለየ ሰው ባንተ ቦታ የሚቆምለት ማነው (2x) አንተ የእኔ ጌታ አንተ ማን ሊተካ አንተ የእኔ አምላክ አንተ የለም ምትክ (2x) ለእኔስ አንተ ነህ መሪዬ የቅርቡ ተጠሪዬ የቅርቡ ተጠሪዬ (2x) ከአንተ ሌላ ለእኔ ማነዉ (2x) ከአንተስ ሌላ ለእኔስ ለምኔ (2x) ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ይጣፍጣል (2x) ፍቅርህ ከማር ወለላም ይመረጣል (2x) ይመረጣል አሃሃ ይመረጣል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection