Song Lyrics

አይበዛብህም

Bethlehem Tezera
Abet Amilake
ገንኖ ገንኖ ስምህ መውጣቱ ፍጥረት ሁሉ ስላንተ ማውራቱ ከፍታ ላይ አለመድረሱ ይሄ ሁሉ ማዕረጉ ልክ ነው አይበዛብህ እንዲያውም ስያንስብህ (3x) ማን ብሎህ ከበርህ አንተ እራስህ ክቡር ማን ሾሞህ ነገስህ አንተ እራስህ ንግስ ማን ብሎህ ክቡር ሆንክ ማን ሾሞህ ነገሥህ (2x) አንተ እራስህ ክቡር ነህ (2x) አንተ እራስህ ንጉስ ነህ (2x) እራስህ አንተ እራስህ ክቡር ነህ እራስህ አንተ እራስህ ንጉሥ ነህ ጌታዬ እኔ ከምልህ አንተ ያለህ ብዙ ነው ስለገረመኝ ብቻ እንዲህ ነህ እልሃለሁ (2x) ምስጋናዬን እሰማለሁ በከንፈሬ የወጣው ግን የሞላው ነው ነው ከልቤ አምልኮዬን እሰማለሁ በከንፈሬ የወጣው ግን የሞላው ነው ከልቤ ከልቤ ነው ከልቤ አይደለም በከንፈሬ (2x) ዝማሬዬን አሰማለሁ በከንፈሬ የወጣው ግን የሞላው ነው ከልቤ አድናቆቴን አሰማለሁ በከንፈሬ የወጣው ግን የሞላው ነው ከልቤ ከልቤ ነው ከልቤ አይደለም በከንፈሬ (2x) ክበር ይላሉ ንገሥ ይላሉ በሰማይ ያሉ በምድር ያሉ ሲሉህ ሰምቼ ልልህ ቆምኩኝ እኔም የራሴ ምሥጋና አለኝ (2x) አለኝ ምሥጋና አለኝ አለኝ ዝማሬ አለኝ አለኝ አምልኮ አለኝ አለኝ አድናቆት አለኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection